በገብር ኄር የጤናና ማኅበራዊ በጎ አድራጎት ድርጅት የማኅበራዊ ክፍል በዓልን ከልጆች ጋር አከበረ

ገብር ኄር ፕሮጀክት ቀርጾ 200 ልጆች በማስተማርና መሠረታዊ ፍላጎታቸውን ለማገዝ ከታኅሣሥ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ አንዱን ወይም ሁለቱንም ወላጆቻቸውን ያጡ ወይም ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ተጋላጭ ሕጻናትና ታዳጊዎችን ያቀፈ ነው፡፡ ድጋፍ ለሚደረግላቸው ታዳጊዎች በየወሩ  600 ብር ከድጋፍ ሰጭዎች ለአንድ ልጅ በመቀበል፤ ተቀብሎም ምንም ሳይቀንስ ቀጥታ ለልጆቹ በመላክ ገብር ኄር ለሀገራችን ልማትና እድገት የራሱን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡ከዚህ በተጨማሪ በአዲሱ ዓመት ልጆች ከቤተሰቦቻቸው ጋር በዓሉን እንዲያከብሩ በማድረግ እና ለአዲሱ የትምህርት ዘመን የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶችን በተወሰኑ ወረዳዎች ለመለገሥ ጥረት ተደርጓል፡፡ እገዛውን በተጠናከረ መልኩ ለመቀጠል ድርጅቱ ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡

Post Views: 294